የዘንዶ ሱባዔ? -----ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

የዘንዶ ሱባዔ? -----ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ
መግቢያ 
ሱባዔ፦ በሰው፤ በቦታና በሰአት ስለሚከናወን የሶስቱም ማለትም የሰአት፤ የሰባዊነትና የመካን ድምር ነው። ሱባዔ በኦርቶዶክስ
ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጥልቅ፤ ረቂቅና ምጡቅ ግንዛቤ አለው። በመንፈሳችንና በሥጋችን መካከል ያለውን ሚዛን አለመሰበሩንና አለማጋደሉን፤
በፈጣሪያችንና በራሳችን መካከል፤ በህዝባችንና በራሳችን መካከል ያለንን ግንኙነት የምንፈትሽበት ነው። በሩቅና በቅርብ ያለውን አካባቢያችንን
ማየት የምንችልበት ተራራ ነው። ውስጣዊ ህሊናችንን የምናይበት ረቂቅ መስታወት ነው። የራቀውን አቅርቦ የረቀቀውን አጉልቶ የሚያሳየን፤
እመቀ እመቃት፡ አየረ አየራት፡ ያሉትን ሁሉ ፍጥረታት የምንፈትሽበት ተራዛሚ መነጽር ነው።