3.0 አላማችን
3.1 ምዕመናን እርስ በርስ በነጻ መንፈስ እየተወያዩ ሃሳባቸውን በመግለጽ ሕጋዊ አስተዳደር እንዲሰፍን ሊያደርጉ የሚችሉበትን መድረክ መፍጠር። 3.2 በቤተ ክርስቲያኗ አስተዳደርና በምዕመናን መካከል በመተማመን ላይ የተመሰረተ ጤናማና መንፈሳዊ ግንኙነት እንዲፈጠር የውይይት መድረክ መክፈት።
3.3 በምዕመናን ተነሳሽነት የተመሠረተውን ይህንን መድረክ ተቀላቅለው በቤተ ክርስቲያናችን ሕግና ሥርዓት እንዲኖር ለሚደረገው ጤናማ እንቅስቃሴ አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ምዕመናንን መጋበዝ። 3.4 ቤተ ክርስቲያናችን በዊኒፔግ ከተቋቋመችበት ከ1994 ጀምሮ በየጊዜው የተፈጸሙትን የታሪክ ድርጊቶችና ሂደቶችን አቀነባብሮ ማዘጋጀትና ሌሎችም ታሪካዊና ጠቃሚ የቤተ ክርስቲያኗን ዶክመንቶች በሥነ ሥርዓት መጠበቅ። 3.5 ቤተ ክርስቲያናችን አንድነቷን ጠብቃ ታፍራና ተከብራ አሁን ላሉት ምዕመናን እንድታገለግል እና እንደዚሁም ለመጭው ትውልድ በክብር እንድትተላለፍ ማድረግ።
3.6 ከ1997 በፊት በሥራ ላይ በነበረው የቤተ ክርስቲያኗ የመተዳደሪያ ደንብ መሠረት በምዕመናን የተመረጠ ብቃት ያለውና ውጤት ያስገኛል ተብሎ የሚታመንበትን አመራር ማቋቋም።
3.0 Our Purpose
3.1 to create a forum for the congregation to discuss and freely air their opinion for the purpose of establishing an administration where law and order prevail; 3.2 to open bidirectional communication channels based on mutual trust for the purpose of creating healthy and spiritual relationships between the church administration and the parishioners;
3.3 to invite church members to join this movement established at grass roots level for the purpose of restoring law and order in our church, and to contribute to its healthy progress;
3.4 to compile, systematically organize and preserve important church documents and the history of events in our church since its establishment in Winnipeg in 1994.
3.5 to maintain the unity, dignity and integrity of the church with the view of rendering it useful for our congregation and preserving it for future generations.
3.6 based on our Church’s bylaws which had prevailed prior to 1997, to establish an effective and dependable leadership consisting of members who shall be elected by the congregation;