30/10/2013 21:30
Page 1 of 3
ሕዝባዊ ስብሰባ
ኦክቶበር 27 2013
በቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደር ችግሮች ላይ ለመወያየት በሰላም፣ ለአንድነትና ለሕግ የበላይነት መድረክ የተጠራው የምዕመናን ስብሰባ ታሪካዊ ነበር ለማለት ይቻላል። ሁሉም ምዕመናንና ሌሎችም ሃሳባቸውን እንዲገልጹ መድረኩ ዕድል ሰጥቶ አስተናግዷል። መድረኩም ደንቦቹንና መግለጫዎቹን ለተሰብሳቢዎቹ አካፍሏል።መድረኩ ያዘጋጀውን ተነሳሽነት ለመደገፍም ሆነ ለመቃወም መምጣታችሁ በጣም ደስ ብሎናል። እንደሚታወቀው የመድረኩ አላማ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሕግና ሥርዓትን ለማስፈን ነው። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የምዕመናን ሙሉ ተሳትፎ ለማስገኘት እንደዚሁም በቤተ ክርስቲያን የተመረጡትም ሆነ ያልተመረጡት አመራሮች ግልጽና ተጠያቂነት የሚሰማቸው ከሁሉ በላይ ደግሞ በምዕመናን ለተቋቋመው የሕግ የበላይነት ተገዥ ለመሆን ሲችሉ ነው።
መድረካችን የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች/ካህናት ምዕመናኑን በመንፈሳዊና ሃይማኖታዊ መንገድ በነጻነት እንዲያገለግሉት እንጂ በቦርድ አባላት መሠራት ያለበት ሥራ ላይ እንዳይጠመዱ ይፈልጋል።
ምንም እንኳ መጀመሪያ ላይ አንዳንድ ወገኖች ባስነሱት ጩኸት ያለመደማመጥ ቢገጥመንም በመጨረሻ ግን ተሰብሳቢዎች ተረጋግተው ስብሰባውን በዲሞክራሲ መንገድ አካሂደናል።
ስብሰባውን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በማመስገን በጸሎት ልንጀምር ብንፈልግም እንቅፋት ለመሆን ተዘጋጅተው የመጡ ግለሰቦች ይህ እንዳይሆን ተቃውመውታል።
በኛ ስብሰባ ለመሳተፍ ለምን እንደፈለገ ባይገባንም፣ ወንድም ዓሊ ሰዒድ ከውድ ባለቤቱ ዓይኔ ጋር በመሆን በመካከላችን ተገኝቶ ነበር።
Meeting
October 27 2013
The public meeting called to discuss the problems of administrative issues last Sunday can be called historic. It provided forum for all members and more to participate in the meeting. Such meeting is a rare occurrence in our church. The Forum has provided its bylaws and its communiqués to public via various media.
It was satisfying to see so many of you came to support or to oppose the initiative of the Forum for Peace, Unity, Law and Order ( FPULO) initiatives to restore law and order in our church. By that to bring about full participation of the parishioners in the life of the church and to make those elected and appointed to become transparent, accountable and above all respect the rules of law as laid down by the parishioners. FPULO also would like the clergy freed to serve the parishioners in the areas of spiritual and other religious related areas, not bogged down by matters that need to be left to the elected board of trustee.
Although the meeting started with some difficulties as exhibited by the oppositions noise and disruptive modes but in the end all calmed down and it was conducted in an atmosphere of democratic discourse.
We wanted to start the meeting with prayer but the group that came with disruptive motive made it impossible.
Page 2 of 3
ስለዚህም በመድረካችን የተለያዩ ሃሳቦችንና አስተያየቶችን የምናስተናግድ መሆናችንን አሳይተናል። ኖቮምበር 3 2013 በሚደረገው በአባ በተጠራው ስብሰባም ላይ እንደሚሳተፍ ተስፋ አለን።
በዚህ ስብሰባ ሃሳቡን ለመግለጽ የተነሳ ሁሉ አሳቡንና አመለካከቱን ከመድረኩ ምንም መቋረጥ ሳያጋጥመው ለመግለጽ ችሏል። እንዲህም ሆኖ የሌሎችን የመናገር መብት ለመንፈግ የሞከሩም ነበሩ።
በስብሰባው ላይ የተነሱ ሃሳቦች።
1) ከቤተ ክርስቲያን ስለታገዱ አባላት፥
ከቤተ ክርስቲያን ለታገዱት ለአራቱ ምዕመናን የተላከው ደብዳቤ ተነቧል። በደብዳቤው ላይ የተለያዩ አስተያየቶችም ተሰንዝረዋል። ብዙዎች ይህንን የእገዳ ደብዳቤ መላኩ አስተዳደሩ የፈጸመው በችኮላ የተወሰነ ከባድ ስህተት ነው ብለውታል። አንዳንዶችም ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ባህልና ሥርዓት ውጭ የሆነ ተግባር ተፈጽሟል ብለዋል።
የመድረኩ አባላት፣ ቤተ ክርስቲያንን የተመለከተ ጉዳይ ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ለሕዝብም ሆነ ወደ አገሪቱ ሕግ ለማውጣት ፍላጎት እንዳልነበራቸው ገልጸዋል። ሰላማዊ ውይይትን የሚጠይቀው ደብዳቤያችን በሁለት የቤተ ክርስቲያናችን ሽማግሌዎች ወደ ቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ ተልኮ ነበር። ይህንንም ሃቅ ሽማግሌዎቹ ራሳቸው ማረጋገጥ ይችላሉ። ይህንን ሃቅ የሚጻረር ውንጀላ ካለ ግን መሠረተ ቢስ መሆኑን ልናረጋግጥ እንወዳለን። ሆኖም የአባላቱ መታገድ የሚገልጸው ደብዳቤ እንደደረሰን እኛም የሕግ አማካሪ ለመያዝ ተገደናል።
2) ቅዱስ ሲኖዶስ በጉዳዩ እንዲገባበት በበኩላችን የወሰድነው እርምጃ።
መድረካችን ለተፈጠረው ችግር መፍትሄ ለመፈለግ ትብብር ጠይቋል። አባቶችም መፍትሄ እንደሚያደርጉልን ተስፋ አለን።
We have also among us Brother Ali Saeed, who was actively involved in the meeting. Although we have no clue why he came to the meeting with his lovely wife Ainy, but we have demonstrated to him that we were prepared to accommodate any opinions about the problem we face in our church. We hope he is also invited to the November 3, 2013 meeting called by Aba and his board.
Every one that stood up to air his/her opinions did so without any interruption from the chair. There were some who tried to deny others the right to express their ideas.
Issues rose at the meeting:
1. Barring members from the church:
The letter that was sent to four of church members was read to all who participated. It was a quiet response but most felt it was a grave mistake from the leadership of the church to resort to such hasty decisions. Even some commented it is unbiblical and also outside of the norm of the EOTC rules. Members of FPULO made it clear that they did not seek to bring any matter of the church to the public nor to the outside law. The letter for peaceful dialogue was sent to the church administration via two elders from our church. These elders can attest to this fact. Any accusation contrary to this is unfounded and baseless. However, once we received the expulsion letter with the threat we sought a legal counsel.
2. Reaching out and appeal to the Holy Synod for intervention
Page 3 of 3
ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ተጨማሪ መረጃዎች ሲደርሱን ለምዕመናን ይፋ እናደርጋለን። በስብሰባው ላይ እንደተገለጸው አንዳንድ ግለሰቦችም ለችግሩ መፍትሄ ለማፈላለግ ቅዱስ ሲኖዶስ በነገሩ እንዲገባበት የየግላቸውን ሙከራ እያደረጉ መሆናቸውን ተገንዝበናል። በበኩላችን እነዚህ ግለሰቦች የሚያደርጉት ሙከራ እያደነቅን ጥረታቸው እንዲሳካላቸው ከልብ እንመኛልን።
አሁን ያለውን አስተዳደር የሚደግፉ ወገኖች ስሜታዊ በሆነ መንገድ መንቀሳቀሳቸውን ታዝበናል። በዚህ አቋማቸው ምንም ቅሬታ የለንም። ሆኖም በመጯጯህ ሳይሆን በሰለጠነና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ሃሳባቸውን
እየገለጹ እንዲወያዩ ጠይቀናቸዋል። ሁሉም ሰው በግልጽ እየታዘበው፣ አንድ ግለሰብ በእጁ አንገትን የመገዝገዝ/የመቁረጥ ምልክት እያሳየ አባላችንን ለማስፈራራት ያደረገውን ተመልክተናል። እንደዚህ መሰሉን የማስፈራራት ታክቲክ በማንኛውም
መልኩ የማንቀበለው ነው። ጉዳዩ እጅግ አሳሳቢ በመሆኑ ለሚመለከታቸው ባለሥልጣናት መተላላፉን ለሁሉም ግልጽ እንዲሆንለት እንፈልጋልን።
የመድረኩ አባላት በሕገ ደንባችን ውስጥ እንዳሰፈርነው ራሳችንን በሰላማዊ መንገድ የምናስተናግድ ምዕመናን ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን በክርስቶስ አንድ አድርገን የምናይ መሆናችንን እንገነዘባለን።ዋናው አጀንዳችን በሕገ ደንባችን ቁጥር 2.0 የተገለጸው ዕይታችን ነው። ስለ ቤተ ክርስቲያናችን ስለ ማኅበረ ሰባችን ስለ መሪዎቻችንና ሽማግሌዎቻችን አምላካችንን የይቅርታ የሰላም የፍቅርና የፍስሐ ልቦና እንዲሰጣቸው እንጸልያለን።
ለሰላም፣ ለአንድነትና ለሕግ የበላይነት ለተቋቋመው መድረክ
We as a group have sought an assistance to remedy our church’s maladministration. We are hopeful we may see some movement of this front. We will update you as more information is available.
As you were aware at our meeting some individuals also involved in their pursuit to get the Holy Synod involved in the resolution of this matter. We truly appreciate their efforts
We truly understand that the emotions are charged mainly from the side that seems to support the administration. We have no qualms with that but we request civilized and peaceful expression of opinions and debating the issues. We have witnessed one opponent was gesturing like cutting some one’s neck and we will not tolerate such intimidating tactics. For your information the matter is referred is to the authorities.
Members of FPULO have pledged as documented in the Bylaw to conduct themselves in a peaceful manner and they see all as brothers and sisters in Christ. Our sole agenda is as put in our vision.
We pray for our Church, church community, leaders and elders and we ask the Almighty for provision of forgiveness, peace, love and joy.
Forum for Peace, Unity, Law and Order