13/11/2011 21:23
1
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን
የቅድስት ማርያም እና የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን
ዊኒፔግ፣ ካናዳ
ሕዳር 5 2004 (November 13, 2011)
Uየአማካሪ ኮሚቴ ጊዚያዊ ሪፖርት
የሪፖርቱ ይዞታ
1. መቅድም
2. መግቢያ
3. የሥራው ሂደት
4. ውይይት የተካሄደባቸው ነጥቦች፤
ሀ. የመግባቢያ ሃሳቦች
ለ. የመወያያ ነጥቦች
ሐ. ለሥራው የሚፈለገው የመሬት መጠንና መሬቱ የሚገኝበት መንገድ
መ. ለቤተ ክርስቲያን እና ለባህል ማዕከሉ የሚሆኑ ሕንጻዎች ማሠሪያ ተስማሚ ሥፍራ
ሠ. ዕቅዱን ለማሳካት የሚያስፈልጉ ነገሮች
5. ኮሚቴው የደረሰበት ስምምነትና ያቀረባቸው አማራጮች
6. ማጠቃለያ
2
1. መቅድም
ይህ ሪፖርት የተጠናቀረው የአማካሪ ኮሚቴው ሲቋቋም ለኮሚቴው የተሰጠውን የመመሪያ ሃሳብ መሠረት በማድረግ ነው።
መመሪያውም ሪፖርቱ የሚቀርበው ለቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር እና የቦርድ አባላት እንደሚሆን አስቀምጧል።
2. መግቢያ
የአማካሪው ኮሚቴ በቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደርና በቤተ ክርስቲያኗ አስተዳደር ቦርድ ተቋቁሟል። እንደዚሁም የኮሚቴው ሊቀ መንበር፣ ጸሐፊ፣ የሕዝብ ግኑኝነት እንደዚሁም ሌሎቹ አባላት በስም በመዘርዘር ተሰይመዋል። ኮሚቴው ሲቋቋም ሰባት አባላት እንዲኖሩት የተደረገ ቢሆንም ከነዚህ ውስጥ አንዱ በስብሰባው ላይ ስላልተገኘ ሥራው በቀረነው ስድስት አባላት ብቻ ተካሂዷል።
የአማካሪው ሥራ የሚያበቃው የቤተ ክርስቲያኗ ሕንጻና ሁለገብ የዕምነትና የባህል ማዕከል ሥራ ሲገባደድ ይሆናል።
3. የሥራው ሂደት
የተሰጠንን ጥሪና ሃላፊነት ለመወጣት ባዛ ያሉ ሰብሰባዎችን አካሂደናል። ከመጀመሪያው አንስቶ በተሰጡን የመመሪያ ሃሳቦች ዋና ዋና ነጥቦች ላይ በማተኮር ሥራችንን አካሂደናል።
ከሁሉ አስቀድሞ ለህንጻው የሚሆን ቦታ በማፈላለግ ላይ ለማተኮር ስምምነት አድርገናል። ይህንንም ዋነኛ ሃሳብ ለማሳካት የተለያዩ የሥራ ክንዋኔዎችን አካሂደናል።
ከዚያም በተገኘው መረጃ ላይ ሰፊ ውይይት በማካሄድ ነገሮችን መልክ ለማስያዝ ሞክረናል። በዚህ የሥራ ሂደት ላይ በአማካሪው አባላት መካከል የታየው ትብብርና ለሥራው የነበራቸው ትጋት እንደ ምሳሌ የሚጠቀስ ነው።
3
የያንዳንዱ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ በጽሁፍ ተይዞ ከቀጣዩ ስብሰባ በፊት ለአባላት ዝግጁ እንዲሆን ስምምነት ላይ ተደርሶ ተግባራዊ ሁኗል። በመጀመሪያ ላይ ቃለ ጉባኤው በአማርኛ ብቻ ይያዝ ነበር። ነገር ግን ለውጭ ጉዳይ አገልግሎት ሲባል ቃለ ጉባኤው በእንግሊዘኛም እንዲተረጎም ተደርጓል። ሊቀ ትጉሃንና ለማ ለዚህ ሥራ ተመድበዋል።
4. ውይይት የተደረገባቸው ነጥቦች፣
ሀ) የመግባቢያ ሃሳቦች
ይህ በአማርኛ የተዘጋጀው የመግባቢያ ሃሳቦች ሰነድ ለያንዳንዱ አባል እንዲደርሰው ተደርጓል። በመቀጠልም የእንግሊዘኛው ቅጂ ለአባላቱ ተሰጥቷል። መመሪያውም ሙሉ በሙሉ ያለ ተጨማሪ ለውጥ ተቀባይነትን አግኝቷል፡፡
ለ) የመወያያ ነጥቦች
ከቤተ ክርስቲያኒቱ የተሰጠንን መመሪያ መከተል እንደሚገባን ተስማምተናል። እንደዚሁም የተሰጠንን የሥራ ድርሻ አዘጋጅተን እንድናቀርብ ወይንም በተወሰነ የጊዜ ገደብ ሪፖርት እንድናደርግ ተስማምተናል።
ለውይይት ስንቀመጥም ማንኛውም አባል ሃሳብ ለመቅረብ አንደሚችልና ይህም በሊቀ መንበሩ ማዕከላዊነት አንዲሆን ተስማምተናል።
ሐ) ለሥራው የሚፈለገው የመሬት መጠንና መሬቱ የሚገኝበት መንገድ
ይህንን ሥራ በተመለከተ ዕውቀት አላቸው የሚባሉ ግለሰቦችን አፈላልገናል። ከከተማው የአስተዳደር ምክር ቤት አባላትና የሥራ ሃላፊዎች የተለያዩ ምክርና ሃሳብ አፈላልገናል። እንደዚሁም ግምት ውስጥ
4
ሊገቡ ይችላሉ ያልናቸውን የተለያዩ ያገለገሉ ሕንጻዎችና መሬት አፈላልገናል።
ስለ መሬቱ ጉዳይ ሰፊ ውይይት ተደርጎ የተለያቱ የመፍትሄ ሃሳቦችም ቀርበዋል። የሚስፈልገው የመሬት መጠን ከ 2 እስከ 3 acres ነው። ይህ ግምት ከህንጻ ኮሚቴው መረጃ ጋር የተገናዘበ ነው። (አባሪ 2 ይመልከቱ)
አሳማኝ የሆነ የሥራ ዕቅድ (Business Plan) ካቀረብን መሬቱ ከከተማው አስተዳደር ሊገኝ አንደሚችል ተገንዝበናል።
ሌላው አማራጭ፣ መሬቱን በገንዘባችን መግዛት ሲሆን ይህ ሁለተኛው አማራጭ ከፍ ያለ ዋጋ ቢጠይቅም፣ የራሱ የሆነ እንደ አስፈላጊነቱ ለመለዋወጥ የሚያስችለን የአተገባበር ጥቅም አለው።
በሌላ በኩልም አሁን ቤተ ክርስቲያኑ የሚገኝበት ቦታ በማልማት፣ ባሁኑ ጊዜ የመኪና ማቆሚያ ሆኖ የሚያገልግለው ቦታ ላይ ሁለገብ የባህል ማዕከል አዳራሽ ለማሠራት ስለሚቻልበት መንገድ ውይይት ተደርጓል። እንደዚሁም የቤተ ክርስቲያኑ አጎራባች ቤቶችና መሬት በመግዛት አሁን በይዞታችን ያለውን ቤተ ክርስቲያን ማስፋፋት ይቻላል በሚለው አማራጭም ተወያይተናል።
የገንዘብ እርዳታን ለማፈላለግ የማኒቶባ መንግሥትና የፌደራል መንግሥትን ማነጋገር እንደሚቻል ተወያይተናል።
መ) ለቤተ ክርስቲያኑና ለባህል ማዕከሉ የሚሆኑ ሕንጻዎች ማሠሪያ ተስማሚ ሥፍራ
ባጠቃላይ መልኩ ሲታይ ለሕንጻዎቹ የሚመረጠው ቦታ የዊኒፔግ ከተማው መሃልና ከከተማው መሃል ከ 10 ኪ ሜ በማይበልጥ ርቀት ላይ መሆን ይኖርበታል። ለዚህ ሃሳብ ምክንያት የተደረገው አብዛኛው የቤተ ክርስቲያናችን አባል የሠፈረው በከተማው መሃልና በዚያ አካባቢ በመሆኑ ነው። ከሌላ አካባቢ የሚመጣውም ምዕመን ቢሆን የህዝብ መጓጓዣ በመጠቀም በቀላሉ ሊደርስበት የሚችል በመሆኑ ነው። ይህ ሃሳብ ለተጨማሪ ውይይት ክፍት ነው።
5
ሠ) ዕቅዱን ለማሳካት የሚያስፈልጉ ነገሮች።
ለሥራችን የተሻለ ውጤት ለማስገኘት እንድንችል በማሰብ የተለያዩ ሃሳቦችን ከውጭ አፈላልገን አግኝተናል። በ Mr. Randi Cage እና በ Ms. Juanita Desouza-Huletey ያቀረቡትን ሃሳብና ምክር ግምት ውስጥ አስገብተናል። ከዚህ በተጨማሪ የአማካሪው አባላት የራሳቸውን ምርምር አካሂደዋል።
ከላይ ከተጠቀሱት ግለሰቦች የተገኘውን ሃሳብና ከራሱ ከኮሚቴው አባላት የፈለቁትን ሃሳቦች በመመርኮዝ ወደፊት ለመራመድና ውጤት ላይ ለመድረስ ያስችሉናል ያልናቸውን ነጥቦች ከዚህ በመቀጠል ተዘርዘረዋል።
ጠቅለል ባለ መልኩ የሚከተሉትን ነጥቦች ለፕሮጀክቱ መሳካት በጣም አስፈላጊ መሆናቸውን አምነንባቸዋል።
1. የሥራ ዕቅድ (Business Plan)
2. መተዳደሪያ ሕግና ደንብ
3. በባለሙያ የተመረመረ የገንዘብ ሪፖርት
4. ሌሎችም በዛ ያሉ የሚያስፈልጉ ነገሮች
ከላይ በዝርዝር የተጠቀሱት ነገሮች፣ የተለያዩ በመንግሥታዊ ሃላፊነት ላይ ያሉትን ባለሥልጣናትን ለማነጋገር ስንሞክር ይዘን እንድንሄድ ከሚያስፈልጉን ዋና ዋናዎቹ ናችው።
(አባሪን 3 ተመልከት)
6
5. ኮሚቴው የደረሰበት ስምምነትና ያቀረባቸው አማራጮች
ሀ. የሥራ ዕቅድ (Business Plan)፣ የመተዳደሪያ ሕግና ደንቡ እንደዚሁም የቤተ ክርስቲያኒቱ የገንዘብ ገቢና ወጭ በአጭር ጊዜ ተዘጋጅቶ መገኘት ይኖርበታል።
ለ. አሁን ያለው የቤተ ክርስቲያን ይዞታ ሊሰፋበትና ሊታደስበት የሚቻልበትን አማራጭ ማፈላለግ። ይህም በአካባቢው ያሉትን ቤቶችና ቦታዎች በመግዛትና አሁን ለመኪና ማቆሚያ የሚያገለግለውን ቦታ በመጠቀም ይሆናል።
መ. ከጎኑ የባህል ማዕክሉ ሊገነባበት የሚያስችል ሰፊ ግቢ ያለው የቤተ ክርስቲያን ህንጻ መግዛት።
ሠ. ሁሉም ኮሚቴዎች የሚገኙበት ስብሰባዎችን በመጥራት ተጨማሪ ምክክር ማካሄድ
ረ. ከላይ (ቁጥር ሀ) የተዘረዘሩት መረጃዎች እንደተጠናቀሩ ያለክፍያ መሬት የሚገኝበትን መንገድ ለማፈላልግ የከተማውን አስተዳደር መጠየቅ።
6. ማጠቃለያ።
የአማካሪው ኮሚቴ ሥራዎችን ለማቀላጠፍ ያካሄዳቸው የተለያዩ የሥራ ክንውኖች ዋነኛው የሕንጻውን ፕሮጀክት የተመለከተ ነው። ስለሆነም፣ አብዛኛውን ጊዜያችንን ያሳለፍነው ለቤተ ክርስቲያናችን ተስማሚ ቦታ ሊገኝ የሚችልበትን መንገድ በማፈላልግ ነበር። ይህ ሃላፊነት ሙሉ ትኩረታችንን የሚጠይቅ መሆኑን ስለምንገነዘብ ሥራውን ዳር ለማድረስ እንተጋለን።
አሁን የሚያስፈልገው ወደፊት ለመቀጠል እንዲቻል ያቀረብነው ሃሳብ በተግባር እንዲተረጎም ማደረግ ነው።
ኮሚቲያችን ከሁሉም ኮሚቴዎች ከቤተ ክርስቲያኑ አስተዳደርና የቦርድ ዳይሬክተሮች ጋር አጠቃላይ ሰብሰባ እንዲካሄድ ከልብ ይደግፋል።
ብርሃኑ ባልቻ
የአማካሪው ኮሚቴ ሊቀ መንበር ሕዳር 5 2004