መልካም መሪ

26/04/2014 13:21

ከፀና በቃሉ

መልካም አመራር ወይም መሪ በብዙ መልኮች ሊገለፅ ይችላል። መልካም መሪ ተከታዮቹ ሊከተሉት የሚችሉበትን መንገድ ወይም ፍላጎት በአዕምሮአቸው የመፍጠር የመቅረፅ ችሎታ ያለው እንደምን እንደሚያካሄድ ወዴት እየመራ እንዳለ፣ለምን እንደሆነ አውቆ የሚያሳውቅ ተረድቶ የሚያስረዳ ቢሆን መልካም ነው። ተከታዮቹ አስተሳሰቡንም ሆነ አቅጣጫውን ተረድተውና ተቀብለው ከተከተሉ በመሪነቱ ተማምነዋል ማለት ነው። ስለዚህ መሪ በምንና ለምን አንደሚያምን ማወቅ ግዴታው ይመስለኛል ለክርስቶስ ምስክሩ ነውና። አንተ መሪ!!! መንፈሳዊ አስተዳዳሪ ነህና ክርስቶስን አንዴት አንደምንከተለው አሳየን። ዋናውና ከሁሉ በላይ ያለው መንፈሳዊ ሕይወት መሪያችን ግን እግዚአብሔር ሲሆን ቃለ ሕይወትን በውስጣችን አሳድሮ ወደ ዋናው አላማ እናነጣጥር ዘንድ እንዲረዳን የሚያፈቅረው ልጁ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ መንገድና ጥበቡን በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ከልባችን ውስጥ እንዲስልብን እንዲያሳድርብን መልካም እረኝነትን አታቆርጥ እስኪ መፀሐፍ ቅዱሳችንን ገልጠን መልካም መሪ ምን ሊመስል እንዲገባው እንመልከት። ፩ኛ ጢሞ. ፫.፩፪ ማንም ኤዺስ ቆዾስነትን ቢሻ መልካምን ስራ ይመኛል የሚለው ቃል የታመነ ነው። የማይነቀፍም ሊሆን ይገባዋል። ነህምያ ፯፣ ፪ ወንድሜን አኒንና የግንቡን አለቃ ሐናንያን በኢየሩሳሌም ላይ ሾምኃቸው እርሱም እውነተኛ ከሌሎቹም ይልቅ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበረ።

መልካም መሪዋች ታማኝነትን ያሳያሉ ማቴ.፳፣ ፪፮ ማንም ከእናንተ ታላቅ ለመሆን የሚወድ የእናንተ አገልጋይ ይሁን።

መልካም መሪ ያገልግሎት ልብ እንጂ የመገልገል አይደለም ፪ኛ ዜ፣ መዋ ፫፪፣፳ ንጉሱም ሕዝቅያስ እና የአሞፅ ልጅ ነብዩ ኢሳይያስ ስለዚህ ፀለዩ ወደ ሰማይም ጮሁ።

መልካም መሪ ልቡ በፀሎት የተመላና በእግዚአብሔር የተማመነ ነው ፩ኛ ዜ፣ መዋ ፪፩፣፰ ዳዊትም እግዚአብሔርን ይህን በማድረግ እጅግ በድያለሁ አሁን ግን ታላቅ ስንፍና አድርጌ አለሁና አለ።

ሐይማኖተ አበው ዘ፫ ምዕት24:25 አንተም መነኩሴ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በመውደድ ከአኃው ጋር በአንድ ልብ ያለህ ከሆንክ የጌታ ደቀመዝሙር ከንፁሐን ሐዋርያት አንድነት ልትቆጠር ብትወድ እውነተኛ መናኝ ሁን። በፍቅር አንተ አብረሀቸው ያለህ ወንድሞች ህ ቀርቶባቸው በዚህ አለም ያለውን ማናቸውንም ያንተ ብቻ እንደሆነ ፈፅሞ አታስብ።

መልካም መሪ በወሰደው እርምጃ ሁሉ ሀላፊነትን መውሰድ ይገባዋል ፩ኛ ቆሮ።፫፣፲፡፩፭ ከተመሰረተው በላይ ማንም ሊመሰርት አይችልም እርሱም ኢየሱስ ነው።

መልካም መሪ አይኑ ሁሌም በእግዚአብሔር ላይ ነው ዳን፣፮፣፲ ቀድሞም ያደርግ አንደነበረ በየእለቱ ፫ጊዜ በጉልበቱ ተንበርክኮ በ አምላኩ ፊት ፀለየ።

መልካም መሪ የሚናገረውና የሚሰራው አንድ ነው ዳንኤልም አንዲህ አይነት ነበር ኢያሱ።፩፣፱ በምትሄድበት ሁሉ አምላክህ ከ አንተ ጋር ነውና ፅና አ ይዞህ አትፍራ አትደንግጥ ብዬ አላዘዝሁህምን?

መልካም መሪ በእግዚአብሔር ይተማመናል ዮሐ፣፫፣፴ እርሱ ሊልቅ እኔግን ላንስ ያስፈልጋል።

መልካም መሪ እራሱን ከፍከፍ አያደርግም ፩ኝ ዮሐ። ፬፣፩ ወዳጆች ሆይ መንፈስን ሁሉ አትመኑ ነገር ግን መናፍስት በእግዚአብሔር ሆነው እንደሆነ መርምሩ ፫ዮሐ።፩፣፲ ስለዚህ እኔ ብመጣ በክፉ ቃል እየለፈለፈ የሚያደርገውን ስራውን አሳስባለሁ ይህም ሳይበቃው እርሱራሱ ወንድሞችን አይቀበልም ሊቀበሎቸውም የሚወዱትን ከልክሎ ከቤተክርስትያን ያወጣቸዋል።

መልካም መሪ ትክክለኛ ያልሆነውን የውሸት ትምህርት ያውቃል ሚክያስ ፫።፩፣፩፩ የያዕቆብ አለቆችና የእስራኤል ቤት ገዢዎች ሆይ እባካችሁ ስሙኝ ፍርድን ታውቁ ዘንድ አይገባችሁምን? መልካሙንም ጠልታችኃል ክፉውንም ወዳችኃል።

መልካም መሪ ደጉንና መልካሙን ስራ ማድረግን ብቻ ነው የሚያውቀው ዕብ።፮፣፩ ስለዚህ የክርስቶስን ነገር መጀመሪያ የሚናገረውን ትተን ወደ ፍፃሜእንሂድ ደግመን አንመስርት።

መልካም መሪ በስራውና በጌታ ቃል እውቀቱም የበሰለና የጠነከረ ነው። ፩ኛ ዜመ። ፩፪፣፩፡፪ በፂቅላግም ከቂስ ልጅ ከሳዖል በተሸሸገ ጊዜ ወደዳዊት የመጡ እነዚህ ናቸው። በሰልፍም ባገዙት ኃያላን መንግስታት ነበሩ። ቀስተኞችም ነበሩ። በቀኝና በግራም እጃቸው ድንጋይ ሊወነጭፉ ፍላፃም ሊወፈውሩ ይችሉ ነበር።

መልካም መሪ ባአዋቂ ነን ባዬች አማፂያን አይደናገጥም እውቀትና ፈሪያ እግዚአብሔር ያላቸውን ያሰልፋል ወይም በእነርሱ ተከቦአልና ምሳ።፩፪፣፩፭ የሰነፍ መንገድ በአይኑ የቀናች ናት ጠቢብ ግን ምክርን ይሰማል።

መልካም መሪን የምንመረምረው እና የምናውቀው እንዴት ነው? ፩ኝ ሳሙ። ፩፮፣፯ ሰው ፊትን ያያል እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል ይህን አንብበህ ለመሪነት ያጨኸውን አይተህ ተረዳ በአነጋገሩ በአለባበሱ በካባላንቃው ወዘተ ሳይሆን ውሳጣዊ ልቡን በማወቅ ነው ስለ መሪዎቻችን የኛ ኃላፊነትስ ምንድር ነው? ዕብ።፩፫፣፩፯ ለዋኖቻችሁ ታዘዙና ተገዙ እነርሱ ስሌትን እንደሚሰጡ አድርገው ይህንኑ በደስታ እንጂ በሀዘን እንዳያደርጉት ይህ የማይጠቅማችሁ ነበርና ስለነፍሳችሁ ይተጋሉ ሮሜ።፩፫፣፩፡፭ ነፍስ ሁሉ ለበላይ ላሉት ባለስልጣኖች ይገዛ ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ስልጣን የለምና ያሉትም ባለስልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው። ስለዚህ ባለስልጣንን የሚቃወም የእግዚአብሔርን ስልጣን ይቃወማል።

ለውጥን ለማምጣት ከአመፅ ይልቅ ከመሪዎች ጋር ተባብራጩ ስሩ።

መልካም መሪዎቻችንን እንዴት ልንከባከባቸው ይገባናል? ፩ኝ ተሰሎ።፭፣፩፪፡፩፫ ወንድሞች ሆይ በመካከላችሁ የሚደክሙትን በጌታም የሚገዟችሁን የሚገስዿችሁንም ታውቁ ዘንድ ስለ ስራቸውም በፍቅር ከመጠን ይልቅ ታከብሮቸው ዘንድ እንለምናችኃለን።

ሐይማኖተ አበው ዘ፫ ምዕት ፪፪፣፩፪ ሕዝባዊ ሆይ አንተ ግን ስለ መስዋእት አቀራረብ ካህኑን ልትንቅፈው ስልጣን የለህም ካህኑ እንዲህ ያለ ስራ ሲሰራ ብታየው ሸሽተህ ወደሌላ ቦታ ሂድ እንጂ አትንቀፈው አት ዝለፈው።

የሙሴ እጆች ግን ከብደው ነበር ድንጋይም ወሰዱ በቦታቸውም አኖሩ እርሱም ተቀመጠበት አሮንና ሆርም አንዱ በዚህ አንዱ በዚያ ሁነው እጆቹን ይደግፉ ነበር ዘፀ። ፩፯፣፲፡፩፫።

ፀልዩለት ዕብ።፩፫፣፩፰፡፩፱ ፀልየልን በነገር ሁሉ ለመልካም እንድንኖር ወደን መልካም ሕሊና እንዳለን ተረድተናልና።

አግዙት ሮሜ።፩፬፣፲ አንተም ወንድምህ ላይ ስለምን ትፈርዳለህ? ወይስ አንተ ደግሞ ወንድምህን ስለምን ትንቃለህ? ሁላችን በክርስቶስ ፍርድ ወንበር ፊት እንቆማለንና።

ለትችትም አትቸኩል ፪ኛ ሳሙ።፩፪፣፩፡፩፫ እግዚአብሔርም ናታንን ወደዳዊት ላከ ወደ እርሱም መጥቶ የተደረገውን ተረከለት መሪዎች በሰሩት ጥፋት ተጠያቂዎች ናቸውና።

አንብቢ ሆይ መፅሐፍ ቅዱስን መሰረት በማድረግ ስለመልካም መሪ የወጠንኩትን ሐሳብ ከመግታቴ በፊት በማለዳ መያዝ በሚል እርእስ በመላከ መንክራት ግርማ ወንድሙ ከተደረሰው መፅሐር ቅፅ 1 ም 7 ገፅ 309 ከእግዚአብሐር ፊት መሸሽ በገንዘብ መመካት ከሚለው ክፍል በጥቂቱ አክልና አበቃለሁ።

"ለመንፈሳዊነታችን ጥንካሬና ጉድለት ወደ ቤተ እግዚአብሔር የገባንበት ጊዜና የ አባቶች ተክለ ሕይወት ውስጥ የሚያሳዩት የ አርዓያነት ፋይዳ የሚወስነው ሲሆን ሌላው የተጠራበት መንፈሳዊ የእምነትና እግዚአብሔርን የመፍራት የንፁህ ሕሊና አምልኮት ፍቅር የያዛቸው ልምዶች አለመኖር ከአለማዊነት ወደ መንፈሳዊነት እንደገና ወደ አልማዊነት መቀያየር የዘመናችን አግልጋዬች ዋንኛው አደጋ ነው ለእንቅልፍም የተሻለ ቦታ እንዲሰጡ የሚያደርገው ይኸው ነው። በሌላ በኩል ለጥቅም ብቻ የሚያገለግሉ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የሚመጡ ችግሮች ከቢሮክራሲው ሰንሰለት ጋር ተጣምሮ በእምነት ላይ ታልቅ ውድቀትና ውስብስብ ችግሮችን አስከትሎል። በ አገራችን ታሪክ ውስጥ ካሉ ትልልቅ ውድቀቶች መካከል አንዱ እንደ ዬናስ ከእግዚአብሐር አምላክ በመሸሽ የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው የሚለውን መንፈሳዊ የሕይወት መርሆን ከመተው ወይም ከመዘንጋት ጋር በተያያዘ የገጠመን ችግር የመጠፋፋቱና የመከዳዳቱ የመወነጃጀለና የመነካከሱ ፋይል እንደመንስኤ የሆነው መጀመሪያ በቤተ እግዚአብሔር አገልጋዬች ውስጥ የተነሳው የመለያየት ጥፋት አሁን ላለንበት የታሪክ ሂደት በር የከፈተ መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው።

መልዐከ መንክራት ግርማ ወንድሙ በዚሁ መፅሐፋቸው ግፅ 324 ይ አባሕር ውስጥ ጩኸት በሚለው ክፍል እንደሚከተለው አስፍረዋል የ አገልጋዬች መንታ ምላስ መሆን የወንጌልን ምስራች ጉዞ በማደናቀፍ በየመድረኩ ላይ የተቀመጠውን ሰው ሁሉ ቲፎዞ እንዲሆን እንጂ በክርስቶስ የሕይወት ማዕድ ከመንፈስ ቅዱስ ኃይል ከቅዱሳን ተስፋና ከ አምልኮት ፍቅር ጋር እንዲተሳሰር አለማድረግ መጏተትና መለየት ማለያየት ጥላቻና ቅራኔን መስበክ ምርጥና ተወዳጅ ቃሎቻችን ሁነዋል። መድረክ ላይ እግዚአብሔርን በትቃርኒው ደግሞ በልባችንና በኑሮአችን ውስጥ የክፋት መንፈስን እናገለግላለን እንግዲህ አገልጋይ ከአውሬ ሆድ ውስጥ ላለመግባት የሚያደርጋቸው ጥንቃቄዎች በሚገባ ለመግንዘብ በቂ ጊዜ መስጠት ያስፈልገዋል። ከሁሉም በላይ የዬናስ ትምህርት አገልጋዬች ቀድሞ በአውሬ ለመበላት የሚሄዱበትን ፍላጎት ያሳየናል ስለዚህ በዚህም ዘመን የክፉ መናፍስት አውሬ የሰው ልጅን ነፍስ አእምሮ ልቦናና ሕሊናን ከእግዚአብሔር በመለየት ከብርሐን ይልቅ ጨለማን ከእውነት ይልቅ ሐሰትን በሕይወቱ ዘመን እንዲለማመድ የሚያደርገው ትግል ካለፉት ከ አባቶቻችን ዘመን ይልቅ የእኛ እጅግ የከፋ ነው።

በትንቢተ ዬናስ ላይ መፅሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን ከንቱነትንና ሐሰትን የሚጠብቁ ምህረታቸውን ትተዋል ዛሬም ደህንነት ከእግዚአብሔር ነው። የአዲስ ኪዳን ተስፋው ደግሞ እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ እንዲሰጣችሁ ልትሄዱና ፍሬ ልታፍሩ ፍሬአችሁም ሊኖር ሾምኋችሁ ዮሐ።፩፭፣፩፮

መሪሆይ እስከመቼ ታንቀላፋለህ፧ ከእንቅልፍህ ንቃ እያልኩ እንደ ንሐስ ደወል(መረዋ) ጆሮህ ላይ አስተጋባለሁ።

ፀና በቃሉ ዊኒ--ቶባ