በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!

27/05/2011 14:26
1
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!
የተወደዱ መምሕራችን የቤተክርስቲያናችን መሪና አስተዳዳሪ እንዲሁም የመንፈስ
አባታችን ቆሞስ አባ ፍቅረሥላሴ ጸጋው፤
የአባታችን ረዳቶችና የቤተክርስቲያናችን አገልጋዮች የሆናችሁት ወንድሞቻችን ሊቀ
ዲያቆናት ደሳለኝ ፤ ዲያቆን ገብረ ትንሣኤ፤ ዲያቆን ሄኖክ፤ ሊቀ ትጉሃን ያሬድ
እንደዚሁም መዘምራን እህቶቼና ወንድሞቼ፤
በአራቱም የምድር ማዕዘናት ተበትነው ለሚገኙት የተዋሕዶ ልጆች የፍቅር፣ የሰላም፣
የአንድነት፣ የእምነትና የጽናት ምሳሌ እንድትሆኑ እግዚአብሔር አምላክ የመረጣችሁ፤
የቅድስት ማርያም ልጆች፤ የቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች የሆናችሁት የደብረገነት
ምዕመናን እህቶቼና ወንድሞቼ፤
እንደምን ሰነበታችሁ? እንደምን አደራችሁ? እንደምን አረፈዳችሁ?
እንኳን ለእናታችንና ለንግሥታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ልደት በስላም
አደረሳችሁ!!
ከዚህ ቀጥዬ ባለፈው ሳምንት አፕሪል 30 / 2011 ላይ የተደረገውን የገቢ ማሰባሰቢያ
የእራት ምሽት (ፈንድ ሬይዚንግ ዲነር) የሚመለከት ዘገባ (ሪፖርት) አቀርባለሁ።
ቲኬቶቹ ተጠናቅቀው ገቢ ስላልሆኑ … በዛሬው ሪፖርት ላይ የሚቀርበው - ባለፈው
አባታችን እንዳሉት - ትልቁ ትርፋችን የሆነው የሰው ኃይል እንቅስቃሴን
የሚመለከተው ዘገባ ይሆናል። የፋይናንስ ሪፖርቱ፤ ቲኬቶቹ ተጠናቅቀው እንደገቡ
ይቀርባል። በዚህ አጋጣሚ ቲኬቶች ለመሸጥ ወስዳችሁ ያላወራረዳችሁ ምዕመናን
ለወንድም ኃይሉ አበበ ወይም ለወንድም ስሎሞን አስቻለው ሪፖርት እንድታደርጉ
እናሳስባለን።
ቅዳሜ አፕሪል 30 2011 የተደረገው የፈንድ ሬይዚንግ ዲነር ዝግጅት በደብራችን
ታሪክ ውስጥ በዓይነቱ የመጀመርያው የነበረ ሲሆን በዚህች ከተማም ሆነ በዲያስፖራው
ታሪክ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ በምሳሌነቱም ለዘላለም ሲጠቀስ የሚኖር ታላቅ ገድል ነው።
በዕለቱ፣ አባታችን እንዳሉት፤ እጅግ በጣም አስቸጋሪ የሆነው ጉዳይ… አዲስ ሕንፃ
የመገንባቱ ሥራ ሳይሆን፤ በልዩ ልዩ አጋጣሚዎች የተራራቁና የተለያዩ ሰዎችን፣ ወደ
አንድነት የማምጣቱ ተግባር ነው። ቅዳሜ አፕሪል 30 2011 የተደረገው ፈንድ
ሬይዚንግ ዲነር ዝግጅት በዊኒፔግ ከተማችን ውስጥ አለ የተባለው ኃይል ሁሉ
የተገኘበት፤ ሁሉም ሰው ቤተክርስትያኗን በሚመለክት በተለይም የአዲሱ
ካቴድራላችንና የባሕል ማዕከላችን ግንባታ ጉዳይ ላይ በፍጹም አንድነት መንፈስ
ተቃቅፎ የታየበት የተቀደስ ዕለት ነበር።
2
ያለፈው ቅዳሜ አፕሪል 30 2011 የተደረገው ፈንድ ሬይዚንግ ዲነር ዝግጅት በዝና
ሲነገር የነበረው የእኛ የደብረ ገነት ቅድስትማርያም ወቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን
ልጆች፤ ፍቅራችን፣ አንድነታችን፣ እምነታችንና ጽናታችን ለዓለሙ ሁሉ በገሃድ
የታየበት ታሪካዊ ዕለት ነበር።
ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በመጀመርያ መልእክቱ ምዕራፍ 2 ቁ 9 ላይ እንዲህ
ብሎ ነበር (አነበዋለሁ)
“እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት
እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ
የተለየ ወገን ናችሁ፤”
አዎን እኛ በዊኒፔግ የደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ወቅዱስ ገብሬኤል ቤተክርስቲያን
ልጆች - ቅዱስ ጴጥሮስ እንዳለው - ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራንን የእርሱን
የአምላካችንን የመድኃኔዓለም ክርስቶስን በጎነት እንድንናገር የተመረጥን ትውልድ፥
ቅዱስ ሕዝቡ፥ ለርስቱ የተለየን ወገኖቹ ነን። እኛን ለዚህ ታላቅ ክብር የጠራን፤ እኛን
ለዚህ ታላቅ ክብር የመረጠን፤ እኛን ለዚህ ታላቅ ክብር የለየን አምላካችን ከዘለዓለም
እስከዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን!!
እኛ በዊኒፔግ የደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ወቅዱስ ገብሬኤል ቤተክርስቲያን ልጆች -
እሱ እራሱ የጠራን አምላካችን በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 5 ቁ 14 - 16
ላይ እንደተፃፈው (አነበዋለሁ)
“እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር
አይቻላትም። 15 መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ
በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል። 16 መልካሙን
ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ
እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።” ብሎ አዝዞናል።
ጌታችን እንዳለው ….እጅግ ከፍ ባለ ተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትምና፤
መብራትንም አብርተው በቤት ላሉት ሁሉ እንዲያበራ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታልና
እስከዛሬ በራሷ አጽርና በራሷ ልጆች ብቻ ተወስና የቆየችው ደብረ ገነት
ቤተክርስቲያናችን ያለፈው ቅዳሜ አፕሪል 30 2011 ብርሃኗ በሰው ፊት ሁሉ
በርቷል!! በዚሁም መልካም ሥራም በሰማያት ያለው አባታችን ከብሯልና ሁላችሁም
ልጆቹ ደስ ይበላችሁ!!
ቤተክርስቲያናችን እስከዛሬ በራሷ አጽርና በራሷ ልጆች ብቻ ተወስና ቆየች ስንል
ባለፈው ቅዳሜ ያደረገችውን ዓይነት ዝግጅት ይዛ ዊኒፔግ ከተማ ውስጥ አልወጣችም
ማለታችን እንጂ እስከዛሬ ከራሷ ክልል ውጭ ምንም ሥራ አልሠራችም፤ እስከዛሬ ከራሷ
ምዕመናን ሌሎችን በፍጹም አላገለገለችም ማለታችን ግን አይደለም።
3
ደብረ ገነት ቤተክርስቲያናችን በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ በዲያስፖራ የተለያዩ አገሮች
የሚታዩና የሚጨበጡ አያሌ ሥራዎችን ሠርታለች፣ ከራሷ ምዕመናን ውጭ የሚገኙ
የብዙ ምዕመናንንም ሕይወት በተጨባጭ ለውጣለች።
በዚህም ምክንያት የደብረ ገነታችን እጅ በጣም ረጅም፤ ድምጿም ሩቅ ተሰሚ፤ ሥራዋም
በዓለም ሁሉ የታወቀና በገሃድ የሚታይ ነው ብለን በሙሉ ልብ መመስከር እንችላለን።
ረጅሙ የደብረ ገነታችን እጅ ባለፉት አሥር አመታት ባደረግናቸው የስፖንሰርሺፕ
እንቅስቃሴዎች በዓለም ዙርያ በስደት ላይ ያሉ ብዙዎች ወገኖቻችንን ከኬንያ፣
ከኡጋንዳ፣ ከሱዳን፤ ከጂቡቲ፣ ከግብጽ፣ ከደቡብ አፍሪቃ ከአውሮጳና እስያ ስደት ምድር
ወደ ነፃነትና አዲስ ሕይወት መርቷል።
ረጅሙ የደብረ ገነታችን እጅ ኢትዮጵያ ውስጥ በረሃብ የተጎዱ ወገኖችን መግቧል፤
የተቸገሩ ገዳማትን፤ አብያተ ክርስትያናትንና አባቶችን ረድቷል።
ረጅሙ የደብረ ገነታችን እጅ ለቤተክርስቲያን አገልግሎት የሚውሉ ንዋየ ቅድሳትን
ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ አብያተክርስትያናት ገዝቶና አቅርቦ በቅድስት ሐገር ብዙ
ቦታዎች ለእግዚአብሔር ክብር የሚሰጠውን አገልግሎት አግዟል።
ሩቅ ተስሚ የሆነው የደብረ ገነታችን ድምጽ በካናዳም ሆነ በልዩ ልዩ የአሜሪካ ግዛቶች
የሚገኙ ምዕመናን፤ ትምሕርት ምክርና ማጽናኛ ባስፈለጋቸው ቁጥር አባታችን ቆሞስ
አባ ፍቅረሥላሴ ጸጋው ጋር ስልክ እየደወሉ የሚያዳምጡትና የሚጠቀሙበት ድምጽ
ሆኗል።
የኛ ደብረ ገነት …እጹብ ድንቅ የሆነች ቤተክርስቲያን ነች!!
በዚህም ምክንያት ልጆቿ ሁላችሁም …. ደስ ይበላችሁ!!
የቅዳሜው አፕሪል 30 2011 ፈንድ ሬይዚንግ ዲነር ዝግጅታችን በቤተክርስቲያናችን
ታሪክ አዲስና የተለየ የሚያደርገው ለመጀመርያ ጊዜ ከቅጽራችን ወጥተን ከተማው
ውስጥ አዳራሽ ተከራይተን፣ ቲኬቶች ሸጠን ወደፊት አዲስ ካቴድራልና የባሕል ማዕከል
ለመገንባት ያለንን ዕቅድ ለሁሉም በይፋ ያወጅንበት በመሆኑ ነው።
የቅዳሜው አፕሪል 30 2011 ፈንድ ሬይዚንግ ዲነር ዝግጅታችን፣ በእለቱ የተገኙት
ሁሉ እንደመሠከሩት እስካሁንም በተደጋጋሚ ሲነገር እንደሚሰማው እጅግ በጣም
የሚያኮራና የተሳካ ነበረ።
ይህ ዝግጅት፤ ጥቂቶች የሠሩት፣ የአንድ ሰሞን ድንገተኛ ደራሽ ግርግር ውጤት
አልነበረም። ረጅም ጊዜ የወሰደ ሰፊ ዕቅድና ዝግጅት የተደረገበት መላ የቤተክርስትያኗ
ልጆች በንቃት የተሳተፉበት ዝግጅት ነበረ። ለወደፊቱ ጉዟችን እንዲረዳን ከዚህ ቀጥዬ
የዝግጅቱን ሂደትና ቅንብር እንደዚሁም የአስፈፃሚዎችን ድርሻ የሚመለከቱ ዋና ዋና
ነጥቦችን አቀርባለሁ።
4
የቅዳሜው አፕሪል 30 2011 ፈንድ ሬይዚንግ ዲነር ….ለአዲሱ ካቴድራልና የባሕል
ማዕከላችን ግንባታ የተቋቋሙት ልዩ ልዩ ኮሚቴዎች - ማለትም ሰባት አባላት ያሉት
በዶክተር ብርሃኑ ባልቻ የሚመራው የአማካሪ ካውንስሉ፤ አሥራ ሦስት አባላት ያሉት
በዶክተር ስጦታው ይርዳው የሚመራው የሕንፃ ኮሚቴው፤ ዘጠኝ አባላት ያሉት
በወንድም ኃይሉ አበበ የሚመራው የአስተባባሪ ቡድኑን አባላት በጋራና በየቡድናቸው
እየተስባሰቡ ሰፋፊ ውይይቶች በማድረግ ያቀዱትና ሕዝቡንም ይዘው ተግባራዊ
ያደረጉት ታሪካዊ ዝግጅት ነው።
ከነዚህ ሶስት አበይት ኮሚቴዎች በተጨማሪ በወጣት ናሆም የሚመራ አሥራአንድ
አባላት ያሉት የወጣቶችና ሕፃናት አስተባባሪ ኮሚቴ ተመሥርቷል። የሰበካው ጉባኤ
መንፈሳዊ አስተዳደር ኮሚቴ ሲጨመርበት በዚህ ዝግጅት ላይ በአጠቃላይ 45
ወንድሞችና እህቶች በኮሚቴ አባልነት ታቅፈው በንቃት ተሳትፈውበታል።
እንደተለመደው ለእነዚህ ኮሚቴዎች የቤትክርስቲያኗ መሪና አስተዳዳሪ አባታችን ቆሞስ
አባ ፍቅረሥላሴ ጸጋው የቅርብ አመራር የሰጧቸው ሲሆን፣ የሰበካው ጉባዔ መንፈሳዊ
አስተዳደርም የአባን ቃል ለማስፈጸም በከፍተኛ ደረጃ ተንቀሳቅሷል።
ለመሆኑ የእነዚህ አዳዲስ ኮሚቴዎች አባላት እነማን ናቸው?
በዶክተር ብርሃኑ ባልቻ የሚመራው የአማካሪ ካውንስሉ አባላት ሊ/ት ያሬድ ፣ ለማ ፣
ነፀረ ፤ መንግሥቱ ፣ ፍጹምና አቻም ሲሆኑ፤
በዶክተር ስጦታው ይርዳው የሚመራው የሕንፃ ኮሚቴው አባላት ደግሞ አብርሃም
ኃይሉ፣ ግርማ ኃ/ገ፣ ሰሎሞን ንጉሴ፣ ወንድሙ ኪዳኔ፣ ዑቑባይ፣ ወይኒቱ መኮንን፣ ገሊላ፤
ጀማይነሽ፣ አፎምያ፣ ራሔል ካሣ፣ ፍሬሕይወት ና ሚሚ አክሎግ ናቸው፤
በወንድም ኃይሉ አበበ የሚመራው የአስተባባሪ ቡድኑን አባላት ደግሞ ስሎሞን
አስቻለው፣ አበበ ላቀው፣ መርዓይ ዓምደማርያም፣ ዊንታ፣ ባሕርነሽ፣ ደስታ፣ ርብቃና አበባ
ጎይቶምን አሉበት።
ማንኛውም ሥራ/ ጥረት …ስኬታማ እንዲሆን / ፍሬ እንዲያፈራ / ውጤት
እንዲያስገኝ/
• ምን ይሠራል? ለምን ይሠራል? እንዴትይሠራል?
• ማን ይሠራዋል? መቼ ይሠራል? …. ለሚሉትና ለመሳሰሉት
ጥያቄዎች የግድ መልስ መስጠት ያስፈልጋል።
በግብታዊነትና ያለዕቅድ የሚሠራ ሥራ ባልታሰቡ ችግሮች የታጠረ፤ አስፈፃሚዎች
ጊዜና ጉልበታቸውን በከንቱ የሚያፈሱበት፤ ጭቅጭቅና መወነጃጀል የሰፈነበት፤ በዚህም
ምክንያት ሥራው ቀርቶ አስፈፃሚዎቹ እርስ በርሳቸው የሚባሉበት ውጤቱም ተልካሻና
የማይረባ ይሆናል።ይህ እንዳይሆን ማኔጅመንት የግድ አስፈላጊ ነው።
5
ማኔጅመንት ማለት ምንድን ነው? ማኔጅመንት ማለት ከላይ እንዳየነው …. ምን
ዓይነት ሥራ? ለምን የሚሠራ? ማን የሚሠራው? እንዴት የሚሠራ? መቼ የሚሠራ?
የሚሉትንና የመሳሰሉትን መሠረታዊ ጥያቄዎች አንስቶ ለነዚህም ከሚሰጡት መልሶች
አንፃር ዝርዝር ዕቅድ የሚያወጣና አፈፃፀሙንም የሚከታተል .. በሂደት ውስጥ
የሚያጋጥሙ ስሕተቶችና ድክመቶችን የሚገመግም … እንዳስፈላጊነቱም የማስተካከያ
እርምጃዎች የሚወስድ አስተዳደራዊ አሠራር ነው።
ጥቂት ደቂቃዎች ቆም ብሎ ማሰብ የብዙ ሰዓታትን ድካምን ይቀንሳል። ከብዙ ሐፍረትና
ውርደት ይሰውራል። ለማቀድና ለመዘጋጀት የማይሻ፤ በግብታዊነትና በዘፈቀደ
እንዳመጣለት መሥራት የሚፈልግ ሰው አንድም በአዕምሮ ስንፍና የተመላ፤ አለያም
ሥራው ሥኬታማ እንዳይሆን አውቆ እንቅፋት የሚደነቅር ተንኮለኛ ብቻ ነው።
የቅዳሜው አፕሪል 30 2011 ፈንድ ሬይዚንግ ዲነር ዝግጅት፣ ደብረ ገነታችን፣
ለራሳቸው ስምና ዝና ሳይሆን ለእግዚአብሔር ክብር ቅድሚያ የሰጡ፤ እራሳቸውን
ለቤተክርስቲያናቸው ሥራና ዓላማ ሙሉ ለሙሉ ያስገዙ፤ የበሰለ አመራር ለመስጠት
አቅሙና ብቃቱ ያላቸው፣ ፍጹም ትሁታን የሆኑ፣ ታዛዦች፣ ታታሪዎችና ትጉህ ሠራተኛ
ልጆች በብዛት እንዳሏት በተግባር አረጋግጧል!!
የፈንድ ሬይዚንግ ዲነሩን ለማቀድ አያሌ ስብሰባዎች ተደርገዋል። ከላይ በስም
ከዘረዘርኳቸው የአዳዲሶቹ ኮሚቴዎች አባላት መኻከል አብዛኞቹ በንቃት
የተሳተፉባቸው እነዚህ ስብሰባዎቻችን በፍጹም ክርስቲያናዊ መንፈስ የተካሄዱ ነበሩ።
ስብሰባዎቹ … በፀሎት ተከፍተው በፀሎት የተዘጉ፤ የተለያዩ ሐሳቦች በመከባበርና
በመደማመጥ የተስተናገዱባቸው ነበሩ።
በስብሰባዎቹ ሂደት ላይ የኮሚቴዎቹ አባላት ከጉንጭ አልፋ ክርክሮች፤ ከጭቅጭቅና
ንትርኮች እርቀው ሐሳባቸውን በተረጋጋና በሰለጠነ መንፈስ ነበር ያቀረቡት። ይህ በራሱ
ትልቅ ድል ሆኖ የሚታይ ነው!! ይኼም…. ዱላ ቀረሽ እንካ ሰላንትያ ከበዛበት፤
በጫጫታ፣ በሁከትና በትርምስ ከተመላው - ፍሬ አልባ - የጭቅጭቅ “ስብሰባ” ጋር
ሲተያይ የጨለማና ብርሃን ያህል ልዩነት አለው። በስብሰባዎቻችን ሂደት …. እኔ
ያልኩት ካልሆነ ሞቼ እገኛለሁ የሚለውን .. ከሱ የተለየ ሐሳብ ያለውን ሰው ሁሉ አባቱን
እንደገደለበት ደመኛ ጠላት የሚቆጥረውን … ቂመኛና አድመኛ ክፉ መንፈስ ..
እግዚአብሔር አምላክ አጠገባችን ድርሽ እንዳይል አስሮልን ነበር።
ይህንን ያደረገልን አምላካችን የተመሰገነ ይሁን!!
የስብሰባዎቹ ሂደት ቁልፍ የሆነ የውጤታችን መነሻና መሠረት እንደመሆኑ ሁሉንም
የኮሚቴዎች አባላት በተለይም ሊቃነመናብርቱን በጉባዔው ፊት እንዳመሰግን
ይፈቀድልኝ!!
6
ኮሚቴዎቻችን በደብራችን ታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ የተደረገውን የቅዳሜ አፕሪል 30
2011 ፈንድ ሬይዚንግ ዲነር በዝርዝር በማቀድ ብቻ ሳይሆን ተግባራዊ ለማድረግም
በግንባር ቀደምትነትና በአርዓያነት ተሰለፈዋል። በዚህም መሠረት ለዝግጅቱ
የሚያስፈልጉትን ወጪዎች በአመዛኙ ከእራሳቸው ኪስ ወጪ አድርገው ነው የሸፈኑት።
በዚህም ኮሚቴዎቻችን ለዝግጅቱ ጊዜያቸውን፤ እውቀታቸውንና ጉልበታቸውን ብቻ
ሳይሆን ገንዘባቸውንም ነበር መስዋዕት አድርገው ያቀረቡት። ከእነሱ የተረፈውንም
ወጪ ምዕመናን እህቶቻቸውና ወንድሞቻቸው እንዲሸፍኑ አስተባብረዋል።
ኮሚቴዎቻችን ያወጡትን ዕቅድ ወደ ተግባር ለመተርጎም በተደረገው
የሥርራእንቅስቃሴም ላይ ምሳሌ በሚሆን ታታሪነት ከማንም በላይ ለፍተዋል፣ ከማንም
በላይ ደክመዋል። ንጹሐንና ትሁታን በመሆናቸውም ሥራና ኃላፊነት ሳይንቁ ፣ ምን
አገባኝ እኔን አይመለከተኝም ሳይሉ፤ ለግል ክብር፣ ስምና ዝና ሳይጨነቁ በፍጹም
ፍቅርና በከፍተኛ ደስታ አገልግለዋል!
በዓለማዊው ሕይወት -ከቤተክርስቲያን ውጭ- በሙያቸው ትላልቅ የክብር ቦታ ላይ
የሚሠሩት እነ ዶክተር ብርሃኑና እነ ኢንጂነር ዶክተር ስጦታውን የመሳሰሉት ወንድሞች
ለክርስቶስ ክብር ኬሻ ሽንኩርትና ሳጥን ለስላሳ ሲሸከሙ፤ ጋርቤጅ እየለቀሙ የጽዳት
ሥራ ሲሰሩ ከማየት በላይ የእምነት ማረጋገጫ ሕያው ምሥክርነት የት ይገኛል?
በዚህ አጋጣሚ ለኮሚቴዎቻችን አባላት በሙሉ ያለንን ከፍተኛ አድናቆትና ልባዊ
ምስጋና በሁላችሁም ስም አቀርባለሁ!! (አንዴ ሞቅ ያለ ጭብጨባ እናድርግላቸው።)
በተለይም ባለፈው ሐሙስና ዓርብ ሴቶች የኮሚቴዎቻችን አባላት፣ ከሌሎች እህቶቻቸው
ጋር በመሆን ከፍተኛ ድካም ያለበትን የምግቡን ዝግጅት ሥራ ተያያዙት። ሐሙስ
ከሰዓት በኋላ ጀምረው እስከ እኩለ ለሊት .. ዓርብ ደግሞ ከጧቱ ጀምረው እስከ እስከ
እኩለ ለሊት ቤታቸውን ትተው፣ ልጆቻቸውን ትተው፣ ሥራቸውን ትተው ያለዕረፍት
ሠሩ። እህቶቻችን ከድካም ብዛት ሰውነታቸው እስኪንቀጠቀጥ ድረስ ነበር የሠሩት።
አንዳንዶቹ እህቶቻችን እስኪያማቸው ነበር የሠሩት። እንደዛም ሆኖ አላጉረመረሙም።
በዚህ ሁሉ አንድም ክፉ ቃልና መማረር ካፋቸው አልወጣም። እህቶቻችን ሁሉንም
በመስማማት፣ ሁሉንም በፍቅርና ሁሉንም በምስጋና ነበር የሠሩት።
ቤተክርስቲያናቸውንና ሕዝባቸውን የሚያኮሩ፤ በእግዚአብሔር አምላክ የተባረኩና እጹብ
ድንቅ የሆኑ ክርስቲያን እህቶች ናቸው ያሉንና ሁላችሁም ደስ ይበላችሁ!!
አባታችን ቆሞስ አባ ፍቅረሥላሴ ጸጋው በተደጋጋሚ ተመላልሰው እህቶቻችን ባርከዋል፣
አበረታተዋል። የአባ በተደጋጋሚ ኪችኑ ድረስ መሄድ ለአገልግሎቱ የሰጡትን ከፍተኛ
ዋጋ፤ ለልጆቻቸው ያላቸውን ፍቅርና ለሥራቸውም የሰጡትን የተለይ አክብሮት ነው
የሚያሳየው።
በዚህ አጋጣሚ እጹብ ድንቅ ለሆኑት ንጹሐንና ቡሩካን እህቶቻችን ያለንን ታላቅ
አክብሮት፤ ከፍተኛ አድናቆትና ከልብ የመነጨ ምስጋና በሁላችሁም ስም አቀርባለሁ!!
(አንዴ ሞቅ ያለ ጭብጨባ እናድርግላቸው።)
7
የመንፈሳዊ አስተዳደሩ ኮሚቴ አባላት፤ የኮሚቴ ሊቃነመናብርትና ሌሎችም አያሌ
ወንድሞች ምግቡ ይዘጋጅ የነበረበት - እዚሁ ቤተክርስቲያናችን ድረስ በተደጋጋሚ
በመመላለስና አንዳንዶቹም አብረው በመዋል፣ አስፈላጊውን ድጋፍ ለእህቶቻችን
ሰጥተዋቸዋል። ባለፈው ሳምንት አባ እንደገለጹት ወንድማችን መንግሥቱ አያሌው
የእህቶቻችንን ሥራ የሚያቀል ከፍተኛና ወሳኝ እገዛ አድርጎላቸዋል።
በዚህ አጋጣሚ እጹብ ድንቅ ለሆኑት ንጹሐንና ቡሩካን እህቶቻችን ድጋፍ ለሰጡት ሁሉ
ልባዊ ምስጋና በሁላችሁም ስም አቀርባለሁ!! (አንዴ ሞቅ ያለ ጭብጨባ
እናድርግላቸው።)
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለሮሜ ሰዎች በላከው መልዕክቱ ም 12 ቁጥር 10
ጀምሮ እንዲህ ብሎ ነበር (አነበዋለሁ)
“በወንድማማች መዋደድ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፤ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ፤ 11
ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ለጌታ ተገዙ፤”
ለፈንድ ሬይዚንግ ዲነሩ በተደረገው እንቅስቃሴ ሁሉ የደብረ ገነት ልጆች ሁሉ በቅዱስ
ቃሉ በታዘዝነው መሠረት በወንድማማችና እህትማማች መንፈስ እርስ በርሳችን
መዋደዳችን፤ እርስ በርሳችን መከባበራችን፤ ለሥራ ከመትጋት አለመለገማችን፤
በመንፈስ የምንቃጠል መሆናችንና ለጌታ መገዛታችን በአደባባይ ለዓለሙ ሁሉ
ታይቷል።
በፈንድ ሬይዚንግ ዲነሩ ላይ እጅግ ብዙ ሥራዎች ነበሩብን፤ እኛም ሥራዎቹን ለይተን
… ሁሉንም በመዋደድ፣ … ሁሉንም በመከባበር፤ ለሥራ ከመትጋት ባለመለገም፤
ለጌታችን መድኃኒታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገዝተን በሞቀ መንፈስና ወኔ
ነበር … ሁሉንም የሠራናቸው።
ለመሆኑ የነበሩብን ሥራዎችን ምን ምን ነበሩ?
ዋና ዋናዎቹን እንመልከት
1. አዳራሽ ማግኘትና መከራየት
2. ሴኩሪቲ ማግኘትና ሪዘርቭ ማድረግ
3. ቲኬትና ፖስተር ዲዛይን ማድረግና ማሳተም
4. ቲ-ሸርት ዲዛይን ማድረግና ማሳተም (ይህንን በሚመለከት በኛ በኩል ቲ-ሸርቶቹን
ዲዛይን አድርገን ለሚያትሙት ብንሰጥም፤ አታሚዎቹ በፈለግነው ጥራት
ስላልሰሩልን - ስላበላሹት - ለሌላ ጊዜ አስተላልፈነዋል። የተበላሸው ቲ-ሸርት
ይህን ይመስላል … ማሳየት)
8
5. ቲኬቶች ማከፋፍልና መሸጥ
6. የልዩ ለዩ ጉዳዮች ግዢ ኪራይና አቅርቦት ማለትም
1. በሬ፤ ዶሮ፣ እንቁላል
2. ሽንኩርት (ነጭና ቀይ)፤ድንች፣ ሰላጣ፣ ቅጠላ ቅጠል፣ ቃርያ
3. በርበሬ፤ ቅመማቅመም፣ ዘይት፣ ቅቤ ፣ አይብ
4. ለስላሳ፣ ውሃ
5. ወይን
6. ካፕስ፣ ፕሌትስ፣ ናፕኪንስ
7. ለሽያጭ የሚቀርቡ ጉዳዮች፣ ለምሳሌ የፀሎት መፃሕፍት፣
መስቀል፣ መቁጠርያ፣ ስዕሎች የመሳሰሉት
8. ወጥ ማሞቅያ
9. የጨረታ ዕቃ
10. ኦዲዮ ቪዥዋል ሲስተም (እስፒከሮች፣ ማይኮች፣
ፕሮጄክተር [ገዛን!!]፣ የፎቶና የዲቪዲ ካሜራዎች ማዘጋጀትና
የመሳሰሉት ይገኙበታል።)
7. የምግብ ዝግጅት ማለትም
1. እንጀራ፣
2. ዳቦ፣
3. የተለያዩ አይነት ወጦችና ሰላጣ፣ ማዘጋጀትና የመሳሰሉት
ይገኙበታል።
8. የአዳራሽ ዝግጅት ማለትም
1. ዲኮሬሽን
2. ጠረጴዛና ወንበሮች ሴት አፕ፣ (ይኼውም ሪዘርቭ መለየት፣
ጠረጴዛዎቹን መሸፈን፣ ለጠረጴዛዎቹ ቁጥር መስጠት)
3. ኦዲዮ ቪዥዋል ሴት አፕ፣(ማይኮችና ስፒከሮች እንደዚሁም
ፕሮጀክተርና ስክሪን ማዘጋጀት)
4. የምግብ ቢፌ ሴት አፕ(የቢፌ ጠረጴዛውንና የምግብ ማሞቅያ
ማቅረቢያዎቹን፤ መመገቢያ ሰሐኖችና ናፕኪንስ ማዘጋጀት)፣
5. የሚጠጡ ነገሮች ሴት አፕ፣(ውሃና ለስላሳ ካፕስ ማቅረብ፣ )
6. የሚሸጡ እቃዎች ሴት አፕ፣(ለሚሸጡ እቃዎች ቦታ መለየት፣
እቃዎቹን መደርደር) እና የመሳሰሉት ይገኙበታል።
9. ትራንስፖርት ማለትም
1. እንጀራውን፣ ወጡን፣ ውሃውን፣ ካፕስ፣ ፕሌትስ፣ ናፕኪንስ፤
ማይኮች ስፒከሮችና ፕሮጄክተሩን፣ የዲኮሬሽን መገልገያዎችን፣
ለወረብ የሚያስፈልጉትን መቋምያ፣ ጽናጽል፣ ከበሮዎችንና
የመሳሰሉትን ነገሮች ማጓጓዝ ይገኙበታል።
9
10. መስተንግዶ ማለትም
1. በር ላይ ቲኬት መሸጥ
2. በር ላይ ቲኬት መቆጣጠር
3. እንግዶችን ተቀብሎ ቦታ ማስያዝ
4. እንግዶች በቅደም ተከተል እራት እንዲያነሱ ማድረግ
5. ለእንግዶች ለስላሳና ውሃ በበቂ ሁኔታ መቅረቡን ማረጋገጥ
6. ቢፌው ላይ እንጀራና ወጦቹ በዝግጅቱ ሂደት ሁሉ
መሟላታቸውን ማረጋገጥ
11. ዝግጅቱ በተያዘለት ፕሮግራም መሠረት መከናወኑን ከመድረክ መምራት
ማለትም
1. ጸሎቱ
2. መዝሙርና ወረቡ
3. የሕፃናቱ ዝግጅት
4. ልዩ ልዩ ንግግሮች
5. እራቱና ጨረታው ሁሉ በተያዘላቸው ዕቅድና ቅደም ተከተል
መሠረት እንዲፈጸሙ ማድረግ
12. ታሪክ መቅረጽ
1. የዝግጀቱን ሂደት በፎቶና በቪዲዮዎች ለታሪክ መቅረጽ
13. በዝግጅቱ ፍፃሜም አዳራሹን ስንረከብ እንደነበረው መመለስ ማለትም
1. አዳራሹን ማጽዳት
2. ጠረጴዛና ወንበሮችን ወደ የመጡበት መመለስ
3. የተረፈውን ምግብና መጠጥ እንዲሁም ብረት ድስቶቹንና
ኮንቴይነሮቹና ሌሎቹንም ዕቃዎቻችንን ሁሉ ወደ ደብረ ገነት
መመለስ
4. ዲኮሬሽኑን፣ ኦዲዮ ቪዥዋል ሲስተሙን፣ መቋምያዎች፣
ጽናጽሎች፣ ከበሮዎችን ሌሎችንም ከቤተክርስትያናችን
ያመጣናቸውን ሁሉ ወደ ደብረ ገነት መመለስ ይገኙበታል።
እስካሁን የተዘረዘረው ዘርፈ ሰፊ ሥራ እጅግ በጣም ብዙ የሰው ኃይል የሚጠይቅ ነበር።
በፈንድ ሬይዚንግ ዲነር ዝግጅታችን ወረቡንና የሕፃናቱን ዝግጅት ጨምሮ ከ160 በላይ
ሰዎች ቀጥተኛ በሆነ መንገድ በንቃት የተሳተፉበት ሲሆን በመቶዎች የሚቆጠሩ
የቀሩትም ምዕመናን ደግሞ ቲኬት በመግዛት… ስለቤተክርስቲያናቸው ዝግጅት ለሌሎች
በማሳወቅና በመሳሰለው መንገድ አስተዋጽዖ አበርክተዋል። ይኽም የሚያሳየው
በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በዝግጅቱ ላይ ተሳትፎ ያላደረገ የቤተክርስቲያናችን ልጅ
አለመኖሩን ነው።
10
የፈንድ ሬይዚንግ ዲነሩ ዝግጅታችን ፤ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ወቅዱስ
ገብርኤል ቤተክርስቲያን ጥቂቶች እንደ ግል ንብረታቸው በሞኖፖሊ ተቆጣጥረዋት ውር
ውር የሚሉባት ሳትሆን በመቶዎች የሚቆጠሩ ልጆቿ በፍቅር የሚያገለግሏት የሁላችንም
የሆነች የጋራ ቤታችን፤ ሁላችንንም በእኩልነት የምታስተናግድ የጋራ እናታችን
መኾኗን በድጋሚ አረጋጧል።
የፈንድ ሬይዚንግ ዲነሩ ዝግጅታችን፤ ማንኛውም ሰው በገዛ ፈቃዱ ራሱን ካላገለለና
ካልለየ፣ ከቤተክርስቲያን ሆን ብሎ በራሱ ፈቃድና ውሳኔ ካልሸሸ በስተቀር፣ በደብረ ገነት
ቅድስት ማርያም ወቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ውስጥ አንድም ባዕድ፣ አንድም
ባይተዋር፣ አንድም የተገለለና አንድም ትርፍ ሰው አለመኖሩን በድጋሚ አረጋጧል።
የፈንድ ሬይዚንግ ዲነሩ ዝግጅታችን፤ እግዚአብሔርን በንጽሕና ለማገልገልና
አገልግለውም በረከትን ለማግኘት ለሚፈልጉ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች ሁሉ የደብረ
ገነት ቅድስት ማርያም ወቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በር ሁልጊዜ ክፍት መሆኑን
በድጋሚ አረጋጧል።
የፈንድ ሬይዚንግ ዲነሩ ዝግጅታችን፤ ደብረገነት ማንንም ከማንም የማትለይ
የሁላችንም ቤተክርስቲያን …. ቆሞስ አባ ፍቅረሥላሴ ጸጋውም … ማንንም ከማንም
የማያበላልጡ የሁላችንም አባት መሆናቸው በድጋሚ አስመስክሯል።
ይህችን የመሰለች ቤተክርስቲያን፤ ይህንን የመሰለ አባት የሰጠን አምላክ የተመሰገነ
ይሁን!!
የዚህ ሪፖርት ዓላማ ለዝግጅቱ አስተዋጽዖ ያበረከቱ እህቶችና ወንድሞችን በስም እየጠሩ
ማመስገን እንደመሆኑ በአልፋቤቲካል ቅደም ተከተል ስማቸው እነሆ ….
# Name Service
1 Abebe
2 Abebech Bendula
3 Abraham Haylu
4 Acham
5 Adanech
6 Afomiya
7 Aheza
8 Aklilu
9 Alem (Z)
10 Alemtsehay Abdi
11 Alfo
12 Alganesh
13 Almaz - Abebe
14 Almaz - Desta
15 Anteneh
16 Ashenafi
11
17 Askale
18 Bahrnesh
19 Beimnet
20 Behailu ከአሜሪካ
21 Belaynesh
22 Beruk
23 Binyam
24 Bosena
25 D/n Desalegn መዝሙር
26 D/n Henok ማታ ሥራ ላይ ነበረ
27 Dagne
28 Daniel Berhanu
29 Desta
30 Dr Berhanu
31 Dr. Sitotaw
32 Efrem
33 Ejigayehu
34 Elena
35 Elsa
36 Emayu
37 Eshetu
38 Eyesus
39 Eyob Aschalew
40 Ezra
41 Fanaye
42 Frehiywet
43 Gelila
44 Genanaw
45 Girma Assefa
46 Girma Habte Gabriel
47 Habtamu Wedajo
48 Hailu Abebe
49 Hailu Belew
50 Hawlte
51 Haylemelekot
52 Haymanot
53 Hirut
54 Jemainesh
55 Kebede (Eyesus)
56 Ketsela
12
57 Ketsela Kassa
58 Kokebe
59 Lidiya Sold 36 tickets!!
60 Lique Tiguhan Yared
61 Maria
62 Mebrahtom
63 Melaku
64 Mengisteab
65 Mengistu
66 Mehari (Aba’s ride)
67 Mekonnen
68 Merhay
69 Mihret
70 Mike
71 Mimi - Asaye
72 Mimi – Zelalem
73 Mulu
73 Nahome
74 Nani
75 Nebiyat
76 Nebiyou Aboye
77 Netsere
78 Rahel Kasa
79 Ribka
80 Rozi
81 Saifu
82 Ruth
83 Saifu’s Son - Eyob
84 Sami
85 Samson (Sunday School)
86 Samson Berhanu
87 Samson Wubneh
88 Selam
89 Shewangizaw
90 Simret O/Micael
91 Solomon Aschalew
92 Solomon Kassa
93 Solomon Negussie
94 Solomon Zemari
95 Suzi
13
96 Tamirat
97 Tedi
98 Tegist
99 Tegist
100 Tegiste
101 Teklu
102 Teref
103 Tesfaye ከብራንደን
104 Tilahun
105 Tirsit
106 Tsehay Ketema
107 Tsehay
108 Tesfanesh
109 Wendimu Kidane
110 Weynitu
111 Winta
112 Yared Abate
113 Yared Tefera
114 Yared Yimer
115 Yeruqe
116 Yeshi
117 Yirga Merhay
118 Zekarias Aschalew
119 Zekarias (Sunday School)
120 Zafu
121 Zena
ለእነዚህ ስማቸው የተዘረዘሩት እህቶችና ወንድሞች በአባና በቤተክርስትያኗ ስም ልባዊ
ምስጋና እናቀርባለን!! ከእነዚህም በተጨማሪ በመሪ ጌታ ቀሲስ ተስፋ አባተ የተመሩት
መዘምራን እህቶቻችንና ወንድሞቻችን በወረብና በመዝሙር፤ በናሆም፣ ያሬድ አባተ፣
ዘካርያስ እና ሳምሶን የተመሩት የስንበት ትምሕርት ቤታችን ወጣቶች ደግሞ
በመዝሙር ደማቅ ተሳትፎ አበርክተዋል። ለነሱም በአባና በቤተክርስትያኗ ስም ልባዊ
ምስጋና እናቀርባለን!!
የቅዳሜው አፕሪል 30 2011 ፈንድ ሬይዚንግ ዲነር ዝግጅታችን ከአንድ መቶ ስድሳ
በላይ ምዕመናን በቀጥታ የተሳተፉበት ዝግጅት ነበር ስንል፤ ማዳነቅና ማጋነን ፈልገን
አይደለም። እንዲያውም ስጋታችን… ሊስቱን ስናዘጋጅ የዘነጋናቸው ወንድሞችና
እህቶች ሊኖሩ ይችላሉ ብለን ነው። ፍርጥ ያለው እውነት ይህ ነው።
14
አንድ መቶ ስድሳ በላይ ምዕመናን በቀጥታ የተሳተፉበት ዝግጅት ነበር ስንል ግን …
የ160ውም አስተዋጽዖ እኩል ነበር፤ የ160ውም ድካም እኩል ነበር ማለታችን
አይደለም። የተሳትፎው መጠን ሊለያይ፤ የድካሙም ብዛት እኩል ላይሆን ይችላል።
የማን ተሳትፎ ይበልጣል? የማን ድካም ይበዛል? የሚለውን ግን ሊመዝን የሚችለው
ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ያገለገሉት ሕያው አምላካቸው ብቻ ነው!! እኛ የምናውቀው
አንድ እውነት አለ … አንድ ሰው ለአምላኩ ከልቡ የሚሰጠው ማንኛውም ስጦታ ወይም
አንድ ሰው ለአምላኩ ከልቡ የሚያበረክትው አገልግሎት በሰዎች ፊት ትንሽ መስሎ
ሊታይ ቢችልም … በእግዚአብሔር ፊት ግን ታላቅና ክቡር ነው።
ይህንን መጽሐፍ ቅዱስ በሚገባ ያረጋግጥልናል። በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 10 ቁጥር
42 ላይ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ቀዝቃዛ ውሃ የሰጠ ዋጋው አይጠፋበትም ብሎ ነው
ያስተማረው። በማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 12 ከቁጥር 42-44 ላይ ጌታችን አንዲት
ሳንቲም የሰጠችውን ሴት ነው በከፍተኛ ደረጃ ያደነቀው!!
የምናመልከው አምላካችን ምንም ያልተደከመበትን በተፈጥሮ የሚገኝ ቀዝቃዛ ውሃ
የሰጠን ሰው ዋጋው አይጠፋበትም ብሎ እያስተማረ፤ የምናመልከው አምላካችን
የመጨረሻ ትንሿን አንዲት ሳንቲም የሰጠችውን ሴት ከሌሎቹ ሁሉ አስበልጦ ካደነቀ ….
ባላቸው አቅምና በተሰጣቸው ድርሻ ቤተክርስቲያናቸውን ያገለገሉት ወንድሞችና
እህቶችን አስተዋጽዖ ለማናናቅና ለማጣጣል ማንም ሥልጣኑ የለውም ብለን
እናምናለን!!
እኛ ሰዎችን እናመስግን ብለን ስንነሳ፤ አንዳንዶች ደግሞ የምስጋናን አስፈላጊነት
በጣፈጡ ቃላት ሊቃወሙ እንደሚችሉ እናውቃለን። ማመስገናችንንም በተለያየ የክፋት
መንገድ የሚተረጉሙ እንዳሉ፤ ምስጋናን ነውር የሚያደርጉ … አመስጋኝና ተመስጋኝ
የለም እያሉ የሚደሰኩሩም እንዳሉ በሚገባ እናውቃለን።
እንዲህ ዓይነት የተዛባ አመለካከት ላላቸው አንድ መሠረታዊ ነጥብ ማስጨበጥ
እንፈልጋለን። ይኼውም ክርስትና ከሌሎች እምነቶች ከሚለይባቸው ባሕርያት ውስጥ
አንዱና ዋነኛው በፍቅርና በምስጋና ላይ የተመሠረተ መሆኑ ነው።
እደግመዋለሁ ክርስትና ከሌሎች እምነቶች ከሚለይባቸው ባሕርያት ውስጥ
አንዱና ዋነኛው በፍቅርና በምስጋና ላይ የተመሠረተ መሆኑ ነው።
ፍቅር በሌለበት … ምስጋና በሌለበት … ክርስትና አለ ብሎ መናገር ዘበት ነው።
ፍቅር በሌለበት … ምስጋና በሌለበት ….ክርስትና አለ ብሎ መናገር ሐስት ነው።
ፍቅር በሌለበት … ምስጋና በሌለበት…. ክርስትና አለ ብሎ መናገር በፍጹም
የማይቻል/ የማይሆን ነገር ነው።
እኛም እንደ ክርስቲያንነታችን ጥላቻና መለያየትን ሳይሆን ፍቅርና አንድነትን፤
መወጋገዝንና መተቻቸትን ሳይሆን ምስጋናና ማበረታታንን ዋና መለያችን አድረገን
እንጠቀማለን። ለዚህ ነው ደብረገነት ቤተክርስቲያናችን ያገለገሉ ልጆቿን በይፋና
በአደባባይ የምታመሰግነው!!
15
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4 / “8 ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥
እግዚአብሔር ፍቅር ነውና። ….20 ማንም። እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን
ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው
እንዴት ይችላል?” ተብሎ ተጽፏል።
እኛ ደግሞ … ከዚህ ተነስተን … ማንም በባሕርዩ ምስጉን የሆነውን፤ እግዚአብሔር
አምላካችን ማመስገናችን አስፈላጊ ነው እያለ አጠገቡ ያሉትን ወንድሞቹንና እህቶቹን
ካላመሰገን ሐሰተኛ ነው … ያያቸውን ወንድሞቹና እህቶቹን ያላመሰገነ .. ያላየውን
እግዚአብሔር እንዴት ሊያመሰግነው ይችላል እንላለን።
ስለዚህ የእኛ ምስጋናችን … ተራ ሽንገላ ሳይሆን… የእኛ ምስጋናችን … የአራዶች
ብልጣ ብልጥ ፉገራ ሳይሆን.. ወይም የእኛ ምስጋናችን … ለይስሙላና ለፎርማሊቲ
የሚደረግ የቃላት ድርደራ ሳይሆን ሳይሆን …የእኛ ምስጋና … ከክርስትና እምነታችን
የመነጨ … ከልባችን ውስጥ የፈለቀ ንጹሕና እውነተኛ ስሜታችን ነው።
በዚህም ምክንያት፤ አሁንም የቅዳሜው አፕሪል 30 2011 ፈንድ ሬይዚንግ ዲነር
ዝግጅት ላይ አስተዋጽዖ ያበረከታችሁትን ሁሉ በደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ወቅዱስ
ገብርኤል ቤተክርስቲያናችን ስም በድጋሚ ከልብ እናመሰግናለን!!
እናንተ መድኃኔዓለም ክርስቶስ በገዛ ደሙ የዋጃትን ቅድስት ቤተክርስቲያኑን፤
በቅንነትና በንጽህና፣ ባላችሁ አቅም ሁሉ አገልግላችኋልና፤ እግዚአብሔር አምላክ
እናተን ልጆቹንና፣ መላ ቤተሰባችሁን በተትረፍረረፈ በረከትና ጸጋ ይሙላችሁ!!
የተወደዳችሁ ክርስትያኖች!!
ኖቬምበር 7 2010 ቀን በትንቢተ ሚክያስ ም 6 ቁጥር 9 ላይ “የእግዚአብሔር
ድምፅ ከተማይቱን ይጠራታል፤” በማለት በተፃፈው መሠረት እግዚአብሔር መንፈስ
ቅዱስ በአባታችን በቆሞስ አባ ፍቅረሥላሴ ጸጋው ላይ አድሮ አዲሱን ካቴድራልና
የባሕል ማዕከል እንድንሠራ እኛን ሲጠራን በከፍተኛ ደስታና እሺ ብለን ነበር
የተቀበልነው።
በትንቢተ ዘካርያስ 7/ 13 ላይ “ እኔ በጠራሁ ጊዜ እነርሱ እንዳልሰሙኝ፥
እንዲሁ እነርሱ በሚጠሩበት ጊዜ እኔ አልሰማም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ
እግዚአብሔር፤” ተብሎ ተጽፏልና፤ እኛ … እግዚአብሔር አምላክ ሲጣራ መስማቱና
እሺ ማለቱ የሚጠቅመው ለኛው ለራሳችን እንደሆነ በሚገባ እናውቃለን።
እኛ ግን ለዚህ ጥሪ የሰጠነው የእሺታ መልስ፣ ፍርሃትና ጭንቀት የወለደው ሳይሆን፤
በክርስቶስ ኢየሱስ አምላክነትና አዳኝነት ካለን ጽኑ እምነትና ለሱ ለአምላካችን ካለን
የጋለ ፍቅር የመነጨ ነው።
16
እኛ ደብረ ገነቶች ለእግዚአብሔር አምላካችን የጥሪ ድምጽ የሰጠነው የእሺታ መልስ
በወሬ ብቻ የሚቀር አለመሆኑን ቃል በገባነው ግማሽ ሚሊዮን በሚደርስ ዶላር፤ እስካሁን
እየከፍልን ገቢ ባደረግነው በብዙ ሺህ የሚቆጠር ዶላር፤ እንደዚሁም ቅዳሜ አፕሪል 30
2011 ባደረግነው ደማቅና ስኬታማ የፈንድ ሬይዚንግ ዲነር ዝግጅታችን አረጋግጠናል።
እኛ … አዲሱን ካቴድራላችንና የባሕል ማዕከላችንን ለመገንባት ከፊት ለፊታችን
የተደቀነው ኃላፊነት ቀላል አለመሆኑን፤ እጅግ በጣም ብዙ ድካምና ሥራ እንዳለበት፣
ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ፣ የጊዜና የጉልበት መስዋዕትነት እንደሚጠይቀን እናውቃለን።
ነገርግን ባለፈው ቅዳሜ ዝግጅታችን እንዳስመስከርነው፤ የፈለገው ድካም፣ የፈለገው
ሥራ፣ የፈለገው የገንዘብ፣ የፈለገው የጊዜና የፈለገው የጉልበት መስዋዕትነት ቢጠይቅ
የተጠየቀውን ሁሉ ከፍለን በአሸናፊነት እንደምንወጣ ቅንጣት ታህል አንጠራጠርም!!
በ1ኛ ዮሐ 5/ 4 ላይ እንደተፃፈው “የሚያሸንፈው እምነታችን ነው።”
አዎን!! የሚያሸንፈው በክርስቶስ ኢየሱስ አምላክነትና አዳኝነት፤ በእናታችንና
ንግሥታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፤ በሊቀመልዓኩ ቅዱስ ገብርኤል
ተራዳኢነት የሚያምነው ተዋህዶ እምነታችን ነው!!
አዎን!! የሚያሸንፈው በማቴ 16/ 18 ላይ “በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን
እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሏትም።” ተብሎ በአምላካችን የተነገረለት
ወልድ ዋህድ ብሎ … የሚመሥከረው ኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ እምነታችን ነው!!
አዎን!! የሚያሸንፈው በዮዲት ጉዲት የአርባ አመት እሳት፤ በግራኝ መሐመድ
የአሥራአምስት አመት ጭፍጨፋ፤ በፖርቲጊዝ ሚሲዮናውያን መሠሪ ጦርነት፤
በኢጣሊያ ፋሺሽቶች ቦምብና የመርዝ ጪስ፤ በዘመኑ ኮምኒስቶች ተንኮልና በመናፍቃኑ
ቅሰጣ ያልተበገረው ንጹሁ ኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ እምነታችን ነው!!
አዎን!! የሚያሸንፈው አክሱም ጽዮንን የገነባው፤ ደብረ ከርቤ ግሼን ማርያምን የገነባው፤
ከአንድ አለት ድንጋይ የላሊበላ ቤተክርስቲያን ያነጸው በመላው ኢትዮጵያ ውስጥ ድንቅ
ድንቅ አብያተ ክርስትያናትንና ገዳማትን የመሠረተው ኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ
እምነታችን ነው!!
ዛሬ በእኛ ልብ ውስጥ የተቀጣጠለው የእምነት እሳት፣ በቅድስት ኢትዮጵያችን ምድር
ለሁለት ሺህ አመታት በአባቶቻችንና እናቶቻችን መንፈስ ውስጥ ሲንቦገቦግ የኖረው
ድል አድራጊው ኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ የእምነት እሳት ነው!! ይህን የእምነት እሳት
ሊያጠፋ የሚችል አንዳችም ኃይል የለም!!
17
እኛ …ሊቀ መልዓኩ ቅዱስ ገብርኤል ረዳታችችን ስለሆነ፣ እናታችንና ንግስታችን
ቅድስት ድንግል ማርያም በሥራችን ሁሉ አብራን ስላለች፤ ጌታችን መድኃኒታችንና
አምላካችን መድኃኔዓለም ክርስቶስ ስለሚመራንና ስለሚያግዘን እንኳን ቀላሎቹ ሰው
ሠራሽ ችግሮች ይቅሩና የገሃነም ደጆች ራሳቸው ሊያቆሙንና ሊገቱን እንደማይችሉ
ፈጽመን እናምናለን!!
እኛ በመጽሐፈ ነህምያ 2/ 20 ላይ እንደተፃፈው “የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፥
እኛም ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን!” ብለን ተነስተናልና ጅምራችን ፍፃሜ
እንደሚደርስ - ወንድማችን ኢንጂነር ዶክተር ስጦታው ይርዳው ዲዛይን አድርጎ
በስክሪን ላይ ያሳየንን አዲሱን የደብረ ገነታችንን ካቴድራልና የባሕል ማዕከል በዕውን
በዓይናችን እንደምናየው - ገብተንም እንደምንቀድስበት - ቅንጣት ጥርጥር የለንም!!
ክብርና ምስጋና ለእግዚአብሔር ይሁን!!